የጋቢ የሳይዝ መመሪያ

እንኳን ደህና መጡ!
በኦንላይን ትክክለኛ ሳይዝዎን ማግኘት በተለይ ደግሞ የተለያዩ የቦንዳ ፋሽን ልብሶችን ሲገዙ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይህ መመሪያ በልበ ሙሉነት እንዲገዙ እና ለእርስዎ ልክ የሚሆኑ ልብሶችን እንዲመርጡ ለመርዳት የተዘጋጀ ነው።

🔑 ዋናው ህግ፦ ልኬቶችን ማረጋገጥ

በማንኛውም የምርት ገጽ ላይ በጣም አስፈላጊው መረጃ የእቃው ትክክለኛ የሴንቲሜትር (ሳ.ሜ) ልኬት ነው
ትክክለኛ ልክዎን ለማግኘት፦

  • ካለዎት ተመሳሳይ ልብስ ጋር ያወዳድሩ፣ ወይም

  • ከሰውነትዎ ልኬቶች ጋር ያነፃፅሩ (ለምቾት የሚሆን ተጨማሪ ቦታ መተውዎን አይርሱ)።


ክፍል 1፦ ሳይዝዎን እንዴት ያገኛሉ?

አማራጭ 1፦ አስቀድመው ካለዎት ልብስ ጋር ማወዳደር (የሚመከር)

  1. ከቁም ሳጥንዎ ውስጥ በደንብ የሚሆንዎትን ተመሳሳይ ልብስ ይምረጡ።

  2. ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ ቦታ ላይ በማንጠፍ ቁልፍ ቦታዎችን ይለኩ፤ ለምሳሌ ደረትን (ከብብት እስከ ብብት ለክተው በሁለት ያባዙት)።

  3. የእርስዎን ልኬት በምርት ገጻችን ላይ ከተዘረዘሩት ጋር ያወዳድሩ።

🧵 አማራጭ 2፦ ሰውነትዎን መለካት

ለስላሳ የመለኪያ ሜትር ይጠቀሙ። ከሌለዎት ገመድ፣ የቻርጀር ገመድ ወይም የጫማ ማሰሪያ ተጠቅመው ከማስመሪያ ወይም ከሚታወቅ ርዝመት ካለው ነገር ጋር ለምሳሌ A4 ወረቀት (30 ሳ.ሜ ርዝመት) ያነጻጽሩ።

ከእቃው ልኬት ጋር ሚያወዳድሩ ከሆነ በደረትዎ ልኬት ላይ ከ5 እስከ 20 ሳ.ሜ ይጨምሩ።

ለትክክለኛ ውጤት፣ ሰውነትዎን ያለ ልብስ ወይም ቀለል ባለ የውስጥ ልብስ ላይ ይለኩ። የመለኪያ ሜርትሩን ሳያጠብቁ ሰውነትዎን ብቻ እንዲነካ አድርገው ይያዙት።

ቁልፍ የሰውነት ልኬቶች፦

  • ደረት – በሰፊው የሰውነትዎ ክፍል ዙሪያ

  • ወገብ – በቀጭኑ የሰውነትዎ ክፍል ዙሪያ

  • ዳሌ – በሰፊው የዳሌዎ እና የቂጥዎ ክፍል ዙሪያ

  • ቁመት – የልብሱን አጠቃላይ ርዝመት ለመገመት ይረዳል።

ክፍል 2፦ የሰውነት ሳይዝ ሰንጠረዦች እና ተጨማሪ ቦታ (“Ease”)

📊 ሰንጠረዦቹን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

ሰንጠረዦቹ የሚያሳዩት የሰውነት ልኬቶችን እንጂ የልብስ ልኬቶችን አይደለም። አጠቃላይ ሳይዝዎን ለማወቅ ይጠቀሙባቸው።

የሴቶች የሳይዝ ሰንጠረዥ

ሳይዝደረት (ሳ.ሜ)ወገብ (ሳ.ሜ)ዳሌ (ሳ.ሜ)
XS78 – 8360 – 6586 – 91
S84 – 8966 – 7192 – 97
M90 – 9572 – 7798 – 103
L96 – 10378 – 85104 – 111
XL104 – 11186 – 93112 – 119
XXL112 – 12094 – 102120 – 128

የወንዶች የሳይዝ ሰንጠረዥ

ሳይዝደረት (ሳ.ሜ)ወገብ (ሳ.ሜ)
XS81 – 8666 – 71
S87 – 9672 – 81
M97 – 10282 – 87
L103 – 10888 – 93
XL109 – 11894 – 103
XXL119 – 124104 – 110

🧘 “Ease” ምንድን ነው እና ለምን አስፈለገ?

ልብሶች በምቾት እንዲንቀሳቀሱ እና በቀላሉ እንዲተነፍሱ ለማድረግ “ease” የሚባል ተጨማሪ ቦታ ይኖራቸዋል።

  • ከሰውነትዎ ልኬት ጋር ሲያወዳድሩ በደረትዎ ልኬት ላይ ከ5 እስከ 20 ሳ.ሜ ይጨምሩ።

  • ይህ ቦታ ለምቾት፣ እንቅስቃሴ እና ለስታይል አስፈላጊ ነው።

👉 ለትክክለኛው ልኬት ለማግኘት ሁልጊዜ በምርት ገጹ ላይ የተዘረዘሩትን የልብሱ ትክክለኛ ልኬቶች ይመልከቱ።


ክፍል 3፦ ጋቢ ልብሶቹን እንዴት እንደሚለካ

ትክክለኛ ልኬቶችን ለእርስዎ ለመስጠት እያንዳንዱን ልብስ ጠፍጣፋ ወይም ዝርግ ቦታ ላይ እንለካለን። በምርት ገጾች ላይ የሚያገኟቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፦

👕 ቶፖች፣ ቀሚሶች እና ጃኬቶች

  • ደረት – ከብብት እስከ ብብት ተለክቶ በሁለት ይባዛል።

  • ርዝመት – ከትከሻው ከፍተኛው ጫፍ እስከ ታችኛው ጫፍ ድረስ።

  • ትከሻ – ከአንዱ የትከሻ ስፌት እስከ ሌላኛው ስፌት ድረስ።

  • የእጅጌ ርዝመት – ከአንገቱ ጀርባ መሃል ጀምሮ፣ በትከሻው ላይ አልፎ እስከ እጅ አንጓ ድረስ።

👖 ሱሪዎች፣ ጂንሶች እና ቀሚሶች

  • ወገብ – በወገብ ማሰሪያው ላይ ተለክቶ በሁለት ይባዛል።

  • ዳሌ – በልብሱ ሰፊው ክፍል ላይ ተለክቶ በሁለት ይባዛል።

  • የውስጥ እግር ርዝመት (Inseam) – ከእግር መጋጠሚያው ስፌት ጀምሮ በእግሩ ውስጠኛ በኩል እስከታች።

  • ርዝመት (Outseam) – ከወገብ ማሰሪያው ላይ ጀምሮ በውጪ በኩል እስከታችኛው ጫፍ።