በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ)

እንኳን ወደ ጋቢ በደህና መጡ! ምርጥ ፋሽንን በቀላሉ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማገዛችን ደስ ብሎናል። ከእኛ ጋር መገበያየት በተመለከተ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልሶቻቸው ከዚህ በታች ቀርበዋል።

  • ጥ1፡ ምን ዓይነት ዕቃዎችን ትሸጣላችሁ?
    መ፡ በአሁኑ ጊዜ ጋቢ ለአዋቂዎች የሚሆኑ ያገለገሉ (ቦንዳ) ልብሶች ላይ ያተኩራል። . እያደግን ስለሆነ ወደፊት ሌሎች የፋሽን ዘርፎችን እና ክፍሎችን እስክናካትት በትግስት እንዲከታተሉን እንጋብዛለን!

  • ጥ2፡ አዳዲስ ዕቃዎችን በምን ያህል ጊዜ ታስገባላችሁ?
    መ፡ በየሳምንቱ ወይም በየሁለት ሳምንቱ አዳዲስ ምርቶችን ወደ ስብስባችን እንጨምራለን! አዳዲስ የገቡ ልብሶች እንዳያመልጥዎ በየጊዜው ይጎብኙን።

  • ጥ3፡ ልብሶቹ በምን አይነት አቋም ላይ ይገኛሉ?
    መ፡ እያንዳንዱን ዕቃ ንጹህ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን እንዲሁም ከባድ ጉድለት የሌለበትመሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ እንፈትሻለን። እንደ ማንኛውም ያገለገሉ ልብሶች ላይ የሚታዩ ቀላል ምልክቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዝርዝር መረጃ የጥራት ቁጥጥር (Quality Control) ገጻችንን ይመልከቱ።

  • ጥ4፡ የአንድን ዕቃ ሳይዝ (Size) እና ቅርጽ (Fit) እንዴት አውቃለሁ?
    መ፡ ትክክለኛውን ልኬት ማግኘት ወሳኝ ነው! ለእያንዳንዱ የልብስ ዓይነት ዝርዝር መለኪያዎችን በሳንቲሜትር (cm) እናቀርባለን። እነዚህን መለኪያዎች በምርት መግለጫው ላይ እንዲሁም በምርቱ ፎቶዎች ውስጥ በሚገኝ የመለኪያ ሰሌዳ ላይ በምስል ተደግፈው ያገኟቸዋልከመግዛትዎ በፊት እነዚህን መለኪያዎች በጥንቃቄ እንዲያዩ አጥብቀን እንመክራለን።. ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ የሳይዝ መመሪያ (Size Guide) ይመልከቱ።

  • ጥ5፡ እንዴት ማዘዝ ወይም ኦርደር ማድረግ እችላለሁ?
    መ፡ በጣም ቀላል ነው! ያቀረብናቸውን ስብስቦች ይጎብኙ፣ የሚወዱትን ዕቃ ወደ ጋሪዎ (Cart) ያስገቡ፣ ከዚያም ወደ ግዢ ማጠናቀቂያ ገጽ ይሂዱ። ትዕዛዝዎን ለማጠናቀቅ የመላኪያ አድራሻዎን ማስገባት ይኖርብዎታል።

  • ጥ6፡ ምን ዓይነት የክፍያ አማራጮችን ትቀበላላችሁ?
    መ፡ በአሁኑ ጊዜ የሚከተሉትን የክፍያ ዘዴዎች እንቀበላለን፡

    • የሞባይል ክፍያ (ቴሌ ብር, ንግድ ባንክ)

    • እቃው ሰረከቡ በጥሬ ገንዘብ

  • ጥ7፡ እስከ የት ድረስ ታደርሳላችሁ? የማድረሻ ዋጋው ስንት ነው?
    መ፡ ትዕዛዞችን አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ አድራሻዎች እናደርሳለን።. የተለያዩ ቋሚ ዋጋ ያላቸው የዴሊቨሪ አማራጮችን እናቀርባለን። እንዲሁም. የተወሰነ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ለሚያወጡ ትዕዛዞች ነጻ ማድረሻ (FREE delivery) እናቀርባለን – ይህ መጠን በግዢ ሂደት ላይ በግልጽ የሚታይ ይሆናል።

  • ጥ8፡ ለማድረስ (ዴሊቨሪ) ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
    መ፡ የሚፈጀው ጊዜ በምርጫዎ ላይ ይወሰናል። ሆኖም ግን ፈጣን ነን! አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ሁሉም ትዕዛዞች ካዘዙበት ሰዓት ጀምሮ በ24 ሰዓታት ውስጥ ይደርሳሉ።

  • ጥ9፡ የመመለሻ ፖሊሲያችሁ (Return Policy) ምንድን ነው?
    መ፡ የእርስዎ ደስታ ለኛ የትራት መለኪያ ነው! የሆነ ችግር ካለ፣ ዕቃዎችን እንዴት መመለስ እንደሚችሉ ለማወቅ ዝርዝር የእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

  • ጥ10፡ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉኝ እንዴት ጋቢን ማግኘት እችላለሁ?
    መ፡ እርስዎን ለመርዳት ዝግጁ ነን! በሚከተሉት መንገዶች ሊያገኙን ይችላሉ፡

መልካም ሸመታ!