ጋቢ ላይ ይሽጡ!

የፋሽን ንግድዎን ያስፋፉ።

የፋሽን ንግድዎ ብዙ ሸማች የሚደርስበት ቀላል መንገድ።

የፋሽን እቃዎችን ይሸጣል? ጋቢ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የኦንላይን ገዢዎችን በመድረስ የእርስዎን አይነት ነጋዴዎች የበለጠ ዊጠታማ እንዲሆኑ ይረዳል። እኛ በአዲስ አበባ ውስጥ የቦንዳ እና የፋሽን ሽያጭን ቀላል በማድረግ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው የኦንላይን መድረክ ነን።

ጋቢን እንደ የኦንላይን የሽያጭ አጋር አድርገው ያስቡት። እርስዎ ምርጥ የፋሽን እቃዎችን ያቀርባሉ፤ እኛ ደግሞ ሁሉንም የኦንላይን የሽያጭ ስራዎችን ለእርስዎ እናከናውናለን። ይህ ለቦንዳ ሱቆች እና ለማደግ ለሚፈልግ ማንኛውም የፋሽን ንግድ ፍቱን ነው።

እንዴት ከጋቢ ጋር አጋር መሆን ይጥቅማል?

ጋቢ ላይ መሸጥ አስተማማኝ የንግድ ውሳኔ ነው፦

  • ብዙ ገዢዎችን ይድረሱ፦ በአዲስ አበባ ውስጥ የፋሽን እቃዎችን ለሚፈልጉ እያደገ ላለው የኦንላይን ገዢዎቻችን ይሽጡ።

  • ሁሉንም ስራ ማለት ይቻላል እኛ እንሰራለን፦
    የኦንላይን ሽያጭ ጭንቀትን ይርሱት! እኛ ፎቶዎችን በባለሞያዎች በመታገዝ እናነሳለን፣ መግለጫዎችን እንጽፋለን፣ እቃዎችዎን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እናከማቻለን፣ ከደንበኞች ጋር እንነጋገራለን፣ ክፍያዎችን እናካሂዳለ፣ እና ትዕዛዞችን እናደርሳለን። ብዙ ጊዜ እና ጥረት እንቆጥብልዎታለን።

  • ገንዘብዎን ይቆጥባሉ፦ የራስዎን ድረ-ገጽ ወይም መተግበሪያ መስራት ሳይጠበቅቦት፣ የኦንላይን ማስታወቂያ እና የማድረስ ስራ ወጪዎች ሳያስፈልግዎ። የእኛን መድረክ መጠቀም ይችላሉ።

  • ሽያጭዎን ያሳድጉ፦ የእኛ የማስታወቂያ ጥረቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ገዢዎችን ወደ ድረ-ገጹ እና መተግበሪያው ያመጣሉ። ለእርስዎ ተጨማሪ ሽያጭን ለማበረታታት እንደ ነጻ ማድረሻ ያሉ ቅናሾችን እንሰጣለን።

  • እርስዎ በዋና ስራዎ ላይ ያተኩሩ፦
    ጊዜዎን በዋናው ነገር ላይ ያሳልፉ – ምርጥ የፋሽን እቃዎችን በማቅረብ። ሁሉንም የሽያጭ ውጣ ውረዶች ለእኛ ይተዉልን።

  • ቀላል እና ፍትሃዊ፦ ሂደታችን ቀላል ነው፣ እና የ8% ኮሚሽናችን ደሞ ግልጽ እና ተመጣጣኝ ነው።

ምን መሸጥ ይችላሉ?

ከፋሽን ጋር የተያያዙ እቃዎችን እንቀበላለን፦

  • አይነቶች፦ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ ቦርሳዎች፣ የጌጣጌጥ እቃዎች (accessories)።

  • አቋም፦ ቦንዳ (ያገለገሉ) እቃዎች ንፁህ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆን አለባቸውእንደ መቀደድ፣ ቀዳዳ፣ የሚታይ እድፍ ወይም መገርጣት ያሉ ትላልቅ ጉዳቶች ሊኖራቸው አይገባም።

እንዴት እንደሚሰራ፦ ለአጋርነት ቀላል መንገድ

  1. በቅድሚያ ያናግሩን፦ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን ወይም ኢሜይል ይላኩልን። ስለ ንግድዎ እና እንዴት አብረን መስራት እንደምንችል እንወያያለን።

  2. ይሁንታ ያግኙ እና አካውንትዎን ይቀበሉ፦ አጋር ለመሆን ከተስማማን፣ የእርስዎን የጋቢ የሻጭ አካውንት እናዘጋጃለን።

  3. እቃዎችዎን ያቅርቡ፦ የመረጧቸውን የፋሽን እቃዎች በአዲስ አበባ ወደሚገኘው አድራሻችን ያድርሱ።

  4. እንፈትሻለን እናዘጋጃለን፦ ሁሉም ነገር ላይ የጥራት ፍተሻ እናረጋለን። ከዚያም ፎቶ አንስተን፣ ለክተን፣ አሽገን እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እናከማቻለን።

  5. እርስዎ ዋጋውን እና ምዝገባውን ያረጋግጣሉ፦ የኦንላይን ምዝገባውን እናዘጋጃለን። እርስዎ ከመለጠፉ በፊት እያንዳንዱን እቃ ፈትሸው የመጨረሻውን የሽያጭ ዋጋ ይወስናሉ።

  6. እቃዎቹ ኦንላይን ይሸጣሉ፦ ደንበኞች እንዲገዙ እቃዎቹን ጋቢ ላይ እናቀርባለን።

  7. ሽያጭዎን ኦንላይን ይከታተሉ፦ በሻጭ አካውንትዎ በኩል የትኞቹ እቃዎች እንደተሸጡ በቀላሉ ይከታተሉ።

  8. ለገዢዎች እናደርሳለን፦ እቃ ሲሸጥ፣ አሽገን በአዲስ አበባ ውስጥ ላሉ ደንበኞች እናደርሳለን።

ዋጋ፣ ኮሚሽን እና አከፋፈል

  • የእርስዎ ዋጋ፦ የእቃዎችዎን የሽያጭ ዋጋ እርስዎ ይወስናሉ።

  • የእኛ ኮሚሽን፦ ጋቢ ከመጨረሻው የሽያጭ ዋጋ 8% ብቻ ይወስዳል።

  • የእርስዎ ገቢ፦ ከሽያጭ ዋጋው 92% እርስዎ ይወስዳሉ።

  • ክፍያ እንዴት እንደሚፈጸም፦ ለተሸጡ እቃዎች በየ15 ቀኑ (በወር ሁለት ጊዜ) እንከፍልዎታለን።

  • የክፍያ ዘዴ፦ በሞባይል ገንዘብ (Mobile Money) ወይም በባንክ ዝውውር ይምረጡ።

  • ዝቅተኛው የክፍያ መጠን፦ ሽያጭዎ ቢያንስ 5,000 ብር ሲደርስ ክፍያዎችን እናካሂዳለን።

  • ያልተሸጡ እቃዎች፦ እቃዎች ለረጅም ጊዜ ካልተሸጡ፣ ስለ አመላለሳቸው ከእርስዎ ጋር እንማከራለን።

አካባቢ፦ ለአዲስ አበባ ገዢዎች አገልግሎት እንሰጣለን

  • በአዲስ አበባ ውስጥ ላሉ ገዢዎች እናደርሳለን።

  • የንግድ ስራዎ በአዲስ አበባ ውስጥ መሆን አይጠበቅበትምነገር ግን እቃዎችዎን እዚህ በሚገኘው ተቋማችን ድረስ ማምጣት መቻል አለብዎት።

አዲስ ደንበኞችን ኦንላይን ለመድረስ ዝግጁ ነዎት?

ጋቢ የፋሽን ንግድዎን ያሳድግልዎት። ከእኛ ጋር አጋር ለመሆን ፍላጎት ካለዎት፣ ያግኙን!

ለውጦችን በተመለከተ ጠቃሚ ማሳሰቢያ

እባክዎ ይህ መመሪያ እና የአጋርነት ውሎቻችን ወደፊት ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ።

  • ማሳወቂያ፦ ስለ ጉልህ ለውጦች በሻጭ ገጽዎ፣ በኢሜይል ወይም በጽሑፍ መልዕክት እናሳውቅዎታለን።

  • ተፈጻሚ የሚሆንበት ቀን፦ ማንኛውም ለውጦች ተፈጻሚ የሚሆኑበት ቀን በዚህ ገጽ ላይ በግልጽ ይለጠፋል።

  • ስምምነት፦ ስለ ለውጦች ካሳወቅንዎት በኋላ አገልግሎታችንን መጠቀሙን መቀጠልዎ (እንደ አዲስ እቃዎችን ማምጣት) የተሻሻሉትን ውሎች መቀበልዎን ያሳያል።

  • አለመስማማት፦ በለውጦቹ ካልተስማሙ፣ እንዴት መቀጠል እንደምንችል ለመወያየት እባክዎ ያግኙን።

ስለአጋርነት ለመወያየት ያግኙን፦

ስልክ: +251-964-431747
ኢሜይል: partners@gabi.et

መልስዎን እጠብቃለን!