እንዴት ነው አጠቃቀሙ?

ጋቢ፣ ከተለመደው ውጣ ውረድ ነጻ የሆነ የፋሽን እቃዎችን በቀላሉ ሚያገኙበት መንገድ ነው። አሰራራችን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ግልጽ እና እምነት የሚጣልበት እንዲሆን ታስቦ የተነደፈ ነው። በዚህ መልኩ ማዘዝ ይችላሉ፡


🛒 ደረጃ 1፦ ምርጫዎቻችንን ያስሱ

እያንዳንዱን እቃ በስታይሉ እና በጥራቱ በጥንቃቄ ስለምንመርጥ፣ ምርጡን ለማግኘት ብዙ መፈለግ አይጠበቅብዎትም።

  • በቀላሉ ያጣሩ፦ ሚፈልጉትን ለማግኘ በሳይዝ፣ በምድብ ወይም በዋጋ በቀላሉ ያጣሩ።

  • የማይደገሙ ምርጫዎች፦ ለወንዶች እና ለሴቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ልዩ የሆኑ የቦንዳ እቃዎችን ያስሱ።

  • አዳዲስ እቃዎች፦ አዳዲስ እቃዎችን በየጊዜው ስለምናቀርብ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለማየት ደጋግመው ይጎብኙን!


📏 ደረጃ 2፦ ትክክለኛ ልክዎን ያግኙ

ምንም አይነት ግምት ሳያስፈልግ በልበ ሙሉነት እንዲገዙ ሚበቃዎትን ሚያገኙበትን መንገድ ቀላል አድርገነዋል።

  • በሳይዝ ክልሎች ይጀምሩ፦ ፍለጋዎን በፍጥነት ለማጥበብ እንደ ትንሽ (Small ‘S’ )፣ መካከለኛ (Medium ‘M’ )፣ ትልቅ (Large ‘L’ ) ያሉ ማጣሪያዎችን ይጠቀሙ።

  • ትክክለኛ ልኬቶችን ይመልከቱ፦ ለትክክለኛ ልኬት፣ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ እቃ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን ዝርዝር ልኬቶች ይመልከቱ። እነዚህ ልኬቶች እቃው ተዘርግቶ (ተነጥፎ) በሴንቲሜትር የተለኩ ናቸው።

  • እገዛ ይስፈልጎታል? እራስዎን እንዴት እንደሚለኩ ወይም ካለዎት ልብስ ጋር እንዴት እንደሚያወዳድሩ ጠቃሚ መንገዶችን ለማግኘት ‘የሳይዝ መመሪያ ገጻችንን’ ይጎብኙ


🛍️ ደረጃ 3፦ ወደ ዘምቢል ይጨምሩ ከዛ ወደ ክፍያ ያምሩ

ያስታውሱ፣ እያንዳንዱ እቃ ልዩ ነው። አንዴ ከተሸጠ፣ አይደገምም።

  • በፍጥነት የእርስዎ ያድርጉት፦ ዘምቢልዎ ውስጥ እቃዎች ሲያቆዩ ተቀማጭ ይደረግሎታል ማለት አደለም። መጀመሪያ ክፍያውን ያጠናቀቀ ሰው እቃውን ያገኛል።

  • ቀላል የክፍያ ሂደት፦ ዝግጁ ሲሆኑ ወደ ክፍያ (ግዢ ማጠናቀቂያ) ገጽ ያምሩ፤ እዚያም በቀላሉ አካውንት መክፈት ይችላሉ። እቃው ሲደርስ በጥሬ ገንዘብ መክፈልን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ዘዴዎችን እንቀበላለን።


🛵 ደረጃ 4፦ እናረጋግጣለን እና እናደርሳለን

ይህ እንከን የለሽ እና ፍጹም የሆነ የማድረስ (ዴሊቨሪ) አገልግሎት ለመስጠት ይረዳናል።

  • የትዕዛዝዎን ማረጋገጥ፦ መጀመሪያ የትዕዛዝ ቁጥርዎን የያዘ የኤስ.ኤም.ኤስ መልዕክት ይደርስዎታል። ከዚያም የጋቢ አባል ደውሎ የማድረሻ ዝርዝሮችዎን ያረጋግጥልዎታል።

  • “መንገድ ላይ ነው” (Out for Delivery) የሚል መረጃ፦ ትዕዛዝዎ ከተረጋገጠ በኋላ፣ እቃው ወደ እርስዎ ጉዞ ሲጀምር ወዲያውኑ ሌላ ኤስ.ኤም.ኤስ ይደርስዎታል።

  • ከአሽከርካሪው ጋር የሚደረግ ግንኙነት፦ ምርጡ አሽከርካሪያችን እርስዎ ያሉበት አካባቢ ሲደርስ የመጨረሻውን ርክክብ ለማቀላጥፍ ይደውልልዎታል።

✨ ደረጃ 5፦ በርዎ ላይ ይሞክሩት እና ይወስኑ

ይሄ ነው ጋቢን ሚለየው፦ እውነተኛ ከስጋት የጸዳ የግዢ ተሞክሮ።

  • ያለዎት ከ10-20 የደቂቃ መስኮት፦ ትዕዛዝዎ እደደረሰ በእቃዎቹ ልኬትና እና ስታል ሙሉ በሙሉ ደስተኛ መሆንዎን ለማረጋገጥ ሲመረምሩ እና ሲሞክሩ አሽከርካሪያችን ይጠብቅዎታል።

  • ልክዎ አይደለም? ችግር የለም። በቀላሉ የማይፈልጓቸውን ለመመለስ ብቁ የሆኑ እቃዎች ለአሽከርካሪው መልሰው ይስጡ።

  • የወደዱትን ያቆዩ፦ አንዴ አሽከርካሪያችን ከሄደ ሽያጩ እንደ መጨረሻ ይቆጠራል። የሚከፍሉት ለማቆየት ለወሰኑት እቃ ብቻ ነው። ለበለጠ መረጃ የእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ። የሆነውን የእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።


💬 ጥያቄ አለዎት?

በኢሜይል አድራሻችን support@gabi.et ይላኩልን ወይም በስልክ ቁጥር +251-964-341747 ይደውሉልን።