ውል እና ሁኔታዎች

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው፦ ነሐሴ 5, 2017 ዓ.ም.

እንኳን ወደ ጋቢ በደህና መጡ! እዚህ በመገኘትዎ ደስተኞች ነን። አካውንት በመክፈት ወይም አገልግሎታችንን በመጠቀም፣ ከዚህ በታች ያሉትን ህግጋቶች እየተቀበሉ መሆኑን ይገልፃሉ።

1. አካውንት እና የብቁነት መስፈርት

  • አካውንት ያስፈልጋል፦ በድረ-ገጻችን ላይ ግዢ ለመፈጸም አካውንት መክፈት አለብዎት። የእርስዎን የአካውንት መረጃ ምስጢራዊነት ለመጠበቅ እና በአካውንትዎ ስር ለሚከናወኑ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች እርስዎ ኃላፊነት ይወስዳሉ።

  • የዕድሜ ገደብ፦ አካውንት ለመክፈት እና ግዢ ለመፈጸም ቢያንስ የ18 ዓመት እድሜ ሊኖርዎት ይገባል። ይህንን ድረ-ገጽ በመጠቀም፣ ህጋዊ ውል ለመፈጸም ብቁ እድሜ ላይ መሆንዎን ያረጋግጣሉ።

2. ትዕዛዞች እና ክፍያዎች

  • የመክፈያ ዘዴዎች፡ ሲደርስ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ ዝውውር እና በቅድመ-ክፍያ የኦንላይን አማራጮችን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ዘዴዎችን እንቀበላለን። የምንጠቀማቸው ዘዴዎች በክፍያ ገጽ ላይ ይቀመጣሉ።

  • ትዕዛዝ በጋቢ መሰረዝ፦ በማናቸውም ምክንያት (ጨምሮ ነገር ግን ሳይወሰን)፦ የእቃ ክምችት እጥረት、የዋጋ ስህተቶች、ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲኖር ትዕዛዝን የመሰረዝ መብታችን የተጠበቀ ነው።

  • ለተሰረዙ ትዕዛዞች ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ፦ እኛ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ትዕዛዝዎን ከሰረዝነው、ሙሉ የገንዘብ ተመላሽ ወደ መጀመሪያው የክፍያ ዘዴዎ ይደረጋል።

3. የእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ

በደንበኛ የሚጀመር ማንኛውም የእቃ መመለስ ሂደት የሚስተናገደው በልዩ የ“በር ላይ መመለስ” አሰራራችን ብቻ ነው። እቃዎች ተቀባይነት ያላቸው በማድረስ ወቅት ብቻ ነው። አንዴ አሽከርካሪያችን ከሄደ፣ ሁሉም ሽያጮች እንደ መጨረሻ ይቆጠራሉ። ስለ ብቁነት፣ ሁኔታዎች እና ገንዘብ ተመላሽ አፈጻጸም የተሟላ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ዝርዝር የሆነውን የእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

4. ማድረስ እና ስጋት

  • የማድረሻ ጊዜ፦ የተገመተው የማድረሻ ቀን እንደ መመሪያ የቀረበ እንጂ የተረጋገጠ አደለም። በሎጂስቲክስ፣ በአየር ሁኔታ ወይም በሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች ምክንያት ለሚፈጠሩ መዘግየቶች እኛ ኃላፊነት አንወስድም።

  • የመጥፋት ወይም የመበላሸት ስጋት፦ አንድ እቃ ለእርስዎ በተሳካ ሁኔታ እስኪደርስ ድረስ ለሚደርስበት መጥፋት ወይም መበላሸት ስጋቱን እኛ እኖስዳለን።

5. የተጠቃሚ ኃላፊነቶች እና የተከለከሉ ድርጊቶች
የሚከተሉትን ላለማድረግ ተስማምተዋል፦

  • የድረ-ገጹን ወይም መተገበሪያ መጥለፍ ወይም መስበር፣ አይፈለጌ መልዕክት መላክ፣ ቫይረሶችን ማስገባት ወይም በሌላ መንገድ ማወክ።

  • ከእኛ በግልጽ የተጻፈ ፈቃድ ሳያገኙ ከእኛ የተገዙ እቃዎችን ለንግድ ዓላማ መልሶ ማዋል።

  • ከድረ-ገጹ መረጃ ለማውጣት ቦቶችን (bots)፣ ስክሬፐሮችን (scrapers) ወይም ሌሎች በራስ-ሰር መሳሪያዎችን መጠቀም።

6. የአዕምሯዊ ንብረት

  • ባለቤትነት፦ ሁሉም አርማዎች፣ የምርት ምስሎች፣ ጽሑፎች እና የድረ-ገጽ ይዘቶች የ Gabi.et ብቸኛ ንብረት ናቸው። ያለፈቃድ መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

  • መቅዳት/መገልበጥ አይፈቀድም፦ ያለእኛ የጽሑፍ ፈቃድ ይዘትን መቅዳት፣ መገልበጥ ወይም ማባዛት ለህጋዊ እርምጃ ይዳርጋል።

7. የአካውንት መዘጋት
በሚከተሉት ምክንያቶች የተጠቃሚ አካውንቶችን ያለማሳወቂያ የማገድ ወይም የማቋረጥ መብታችን የተጠበቀ ነው (እነዚህን ጨምሮ ነገር ግን ሳይወሰን)፦

  • የማጭበርበር ድርጊት (ለምሳሌ፦ የክፍያ ማጭበርበር፣ የውሸት አካውንት መፍጠር)።

  • እነዚህን የአገልግሎት ህግጋት መጣስ።

  • በድረ-ገጹ እና መተግበሪያ ወይም በሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ማንኛውም ባህሪ።

8. ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ክስተቶች (Force Majeure)
ከእኛ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ለሚፈጠሩ መዘግየቶች ወይም ውድቀቶች ተጠያቂ አንሆንም፤ ይህም የኃይል መቆራረጥን፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን፣ የአገልግሎት አድማዎችን ወይም የመንግስት ገደቦችን ያካትታል።

9. የፖሊሲ ማሻሻያዎች
እነዚህን ህግጋት በማንኛውም ጊዜ ልናሻሽል እንችላለን። ለውጦች በድረ-ገጹ ላይ ከተለጠፉበት ጊዜ ጀምሮ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናሉ። ከማንኛውም ለውጦች በኋላ ድረ-ገጹን መጠቀም መቀጠል አዲሶቹን ህግጋት መቀበልዎን ያሳያል።

10. ተያያዥ ፖሊሲዎች እና የህግ ተገዢነት

  • የተቀናጁ ፖሊሲዎች፦ እነዚህ ህግጋትየእቃ እና የገንዘብ ተመላሽ ፖሊሲያችን እና ከግላዊነት ፖሊሲያችን ጋር ተቀናጅተው ይሰራሉ።. በእነዚህ ህግጋት በመስማማት፣ በእነዚያ ፖሊሲዎች ህግጋትም ጭምር መስማማትዎን ያረጋግጣሉ።

  • የኢትዮጵያ ህግ፦ እነዚህ ህግጋት ከኢትዮጵያ አግባብነት ካላቸው ደንቦች ጋር ተጣጥመው የተገነቡ ናቸው።

ያግኙን፦
ለጥያቄዎች በኢሜይል አድራሻችን support@gabi.et ወይም በስልክ ቁጥር +251-964-341747ያግኙን።