ስለ ጋቢ

ሁላችንም ተመሳሳይ ፈተና አጋጥሞናል፤ በአንድ በኩል በውድ ዋጋ አዲስ ልብስ ለመግዛት በጀታችንን መፈታተን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በተለመደው የቦንዳ ግብይት ውጣ ውረድ ማለፍ። ጊዜ የሚፈጀው ፍለጋ፣ አጠራጣሪው ጥራት፣ እና የማይገመተው ተለዋዋች ዋጋ የተለመዱ ችግሮች ነበሩ። የምንወደውን ፋሽን ለማግኘት የተሻለ እና ቀላል መንገድ መኖር እንዳለበት እናስብ ነበር።

መፍትሄው ጋቢ ነው።

እንኳን ወደ ጋቢ በደህና መጡ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት ያላቸው እና የሚያማምሩ የፋሽን ልብሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የተቋቋመ የመጀመሪያው የኦንላይን መድረክ ነው። የፋሽን ግብይት ውጣ ውረዶችን በመቅረፍ ግብይቱን ቀላል፣ እምነት የሚጣልበት እና እጅግ በጣም ምቹ ለማድረግ እዚህ ተገኝተናል።

እኛን ለየት የሚያደርገን ምንድን ነው?

  • እምነት የሚጣልበት ጥራት፦ እኛ ጋር የሚገኝ እያንዳንዱ እቃ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን እና ለመልበስ ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ ይመረመራል። ሙሉ በሙሉ ግልጽነት ላይ ስለምናምን፣ ሁልጊዜ ግልጽ ፎቶዎችን እና ትክክለኛ መግለጫዎችን ወይም ማብራሪዎችን ያገኛሉ።

  • በእውነተኛ ተመጣጣኝ ዋጋዎች፦ ምርጥ ስታይልን ማግኘት ኪስን የሚጎዳ መሆን የለበትም ብለን ስለምናምን ዋጋዎቻችንን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እናወጣለን። ፋሽንን በጀትዎ ጋር ተስማሚ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን።

  • በየትኛውም ጊዜ፣ ከየትኛውም ቦታ የእኛ መድረክ ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ልዩ የሆኑ እቃዎችን በማንኛውም ጊዜ፣ ከየትኛውም ቦታ አዲስ አበባ ውስጥ በቀጥታ ወደ አሉበት የዘዙ።

  • ያለምንም ስጋት በልበ ሙሉነት ይሸምቱ፦ የእርስዎ እርካታ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ግልጽ የሆነው መመለሻ እና የመለወጫ ፖሊሲያችን ሁልጊዜ በልበ ሙሉነት መሸመት እንደሚችሉ ያረጋግጥልዎታል።

ጋቢ፣ በአዲስ አበባ ውስጥ ጥራትን ለሚፈልጉ፣ የኦንላይን ግብይትን ምቾት ለሚወዱ እና ውድ ዋጋ ሳይከፍሉ ምርጥ ስታይልን ለሚፈልጉ ሁሉ ነው።

ጋቢ | የኪስዎ ምርጥ ወዳጅ!

የፋሽን ግብይትን ለማህበረሰባችን አስደሳች እና ተደራሽ ማድረግ ምኞታችን ነው።

የጋቢን ለመሞከር ዝግጁ ነዎት?

‘ይሸምቱ’ የሚለውን ክፍል በመጎብኘት ምርጫችንን ያስሱወይም የፋሽን ንግድ ካለዎት ‘በጋቢ ላይ ይሽጡ’ በሚለው ገጽ ላይ ስለ ፕሮግራማችን ያንብቡ።